Saterday, 09/ 06 /2016
GHC BLOGS
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር በ2001 ዓም ሥራ የጀመረው ጎሮ ጤና ጣቢያ ከ52,779 በላይ ለሚሆን የ02 ቀበሌና አካባቢው ህብረተሰብ የጤና
አገልግሎት እየሰጠ ያለና በዓመት ከ100ሺ
በላይ ተገልጋዮችን እያስተናገደ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
ጤና ጣቢያው የአገልግሎት አድማሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማስፋት የተኝቶ ህክምናን ጨምሮ ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን የአገልግሎት ስብጥርና ጥራት በማሻሻል
ከፍተኛ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ ነው፡፡
አሁን ደግሞ የህብረተሰቡን ፍላጎት ከፍ ባለ ደረጃ ለማሟላትና ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር ተያያዥ በሆነ የጤና ችግር የሚከሰትን የእናቶች ሞት ለመከላከልና
ለመቀነስ የሚያስችለውን የተቀናጀ
ድንገተኛ ቀዶ ህክምናና በቀዶ ህክምና ማዋለድ አገልግሎት በመስጠት አገልግሎቱን ዛሬ ቀን 09/06/2016 አቶ ገዛኸኝ ታዲዮስ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ
ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና
የጤና ጣቢያው አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፅጌሬዳ ክፍሌ፣ አቶ ዩሱፍ ሰይድ የጤና ቢሮ ም/ኃላፊ፣ አቶ አቤል ምስራቅ የወረዳ2 ዋና
ስራ አስፈፃሚ፣ ወ/ሮ ሰላም ፍቅሬ
የወረዳ2 ጤና ማስተባበሪያ ኃላፊና የጤና ጣቢያው አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ፣ የጤና ጣቢያው አመራር ቦርድ አባላትና የህብረተሰብ ተወካዮች እና ሌሎች የጤና
ቢሮ፣ የመንግስት ጤና ተቋማትና
የወረዳ2 አመራሮች በተገኙበት በይፋ ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ አስጀምሯል።
ለአገልግሎቱ መጀመር ደጋፍ ላደረጉት የድልጮራ ሆስፒታል፣ ጤና ቢሮ፣ ቢዮአዋሌና ደቻቱ ጤና ጣቢያዎች ሁሉም ለስራው መሳካት ድጋፍና ትብብር ላደረጋችሁልን
አካላት በሙሉ በተቋማችን ስምና
በተጠቃሚው ማህበረሰብ ስም ከልብ እናመሰግናለን! ክብረት ይስጥልን!
በቀን 17/08/2017 ዓ.ም
በርካታ እስታፎቻችን የተሳተፉበት የደም ልገሳ መረሀ ግብር አንድም እናት በደም እጦት መሞት የለባትም!
በዚህ መረሀ ግብር የተሳተፋቹ ባለሙያዎች እናመሰግናለን
በቀን 02/04/2016 ዓ.ም
በርካታ እስታፎቻችን የተሳተፉበት የደም ልገሳ ፕሮግራም ያዘጋጀን ሲሆን በዚህም በቅርብ የነበረው የዴንጊ
ትኩሳት ተፅዕኖ ቢያሳድርብንም 22 units ደም መለገስ ተችሏል።
በቀን 01/04/2016 ዓ.ም
ተቋማችን ያለውን የወባ መከላከልና መቆጣጠር ያለበትን ደረጃ ለማየት የመጡ የ"USAID`` የጤና
ሚኒስቴር ተወካዮችን ተቀብለን አስተናግደናል። በዚህም የወባ በሽታ
መከላከልና መቆጣጠር
ፕሮግራሞች ትግበራ እና የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና ረገድ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር አስረድተናል።
በቀን 05/24/2016 ዓ.ም
ቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ አዲስ የድንገተኛ ቀዶ ህክምናና በቀዶ ህክምና ማዋለድ (C/S & Emergency
Surgery) አገልግሎት መስጫ ቴብል (New OR Table)
ሰጦናል።
በቀን 05/12/2016 ዓ.ም
የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከላከል ና ለመቆጠጣጠር ወረርሽኙ በተገኝበት አካባቢ የመከላከል ስራ ተሠርቷል
ዛሬ ቀን 29/03/2016 ዓ.ም
ሁለት ፕሮግራሞችን አንድ ላይ በማቀናጀት ከጠቅላላ እስታፎች ጋር አከናውነናል።
1ኛ) የተቋማችንን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግመናል።
በዚህም ሁሉም ኬዝ ቲሞችና ዲፓርትመንቶች አስተባባሪዎች የየክፍላቸውን የ3ወር አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በጋራ
ሰፊ ውይይት