Saterday, 02/13/2016
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በተካሄደ የ2016 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ ተቋማችን ጎሮ ጤና ጣቢያ በበጀት ዓመቱ በከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል በጤና አገልግሎት አሰጣጥ በ1ኛ ደረጃ ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመዝገብ የእውቅና ምስክር ወረቀትና ሜዳልያ ሽልማት ተቀብለናል፡፡
Congratulations all!
Goro PHCU Always one Step a Head!
Saterday, 6/07/2017
ጎሮ ጤና ጣቢያ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ለማሻሻል እና የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ ይቻል ዘንድ ለባለሙያዎቹ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱን ቀጥሏል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ላይ በተግባር ልምምድ የታገዘ ስልጠና (Basic Emergency Care Training) ሰጠናል። ስልጠናው 15 Credit hour ያለው በመሆኑ ለባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን CPD ለማሟላት የሚያግዝ ተጨማሪ ጠቀሜታ ያለው መሰረታዊ ስልጠና ነው። ስልጠናውን ያስተባበረልንን ጤና ቢሮ በተለይ ደግሞ ተሬሳ እና ስልጠናውን የሰጡልን የድል ጮራ ሆስፒታል ባለሙያዎች (ዘላለምና ልሳኑ) ከልብ እናመሰግናለን! በቀጣይም ተቋማችን ጎሮ ጤና ጣቢያ ''ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት በጥራት'' የሚለውን መሪ ቃሉን በተግባር ለማረጋገጥ እንደ ንብ የሚሰሩ እስታፎቹን ይዞ ይተጋል።
Saterday, 29/06/2017
በጎሮ ጤና ጣቢያ በቀን 29-30/06/2017 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተቋሙ አዘጋጅነት በተቋሙ ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች በ Non-Communicable Disease(NCD) Care ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰቷል። በዚህም መሰረት የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግና ለሕብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመሰጠት ተቋማችን በትኩረት ይሰራል።
Saterday, 20/11/2016
ጎሮ ጤና ጣቢያ በቀን 20/11/2016 ዓ.ም የጠቅላላ ሰራተኞች ስብሰባ መድረክ በማዘጋጀት የተቋማችንን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ዓመታዊ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ የተካሄደ ሲሆን የተቋሙ ዓመታዊ አፈፃፀም ዝርዝር ሪፖርት በኬዝ ቲም ደረጃ በመድረኩ ቀርቦ ውይይት አድርገናል። በዚህም ከቀረበው ሪፖርት በተጨማሪ በመድረኩ በበጀት ዓመቱ...
Saterday, 09/ 06 /2016
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር በ2001 ዓም ሥራ የጀመረው ጎሮ ጤና ጣቢያ ከ52,779 በላይ ለሚሆን የ02 ቀበሌና አካባቢው ህብረተሰብ የጤና አገልግሎት እየሰጠ ያለና በዓመት ከ100ሺ በላይ ተገልጋዮችን እያስተናገደ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ጤና ጣቢያው የአገልግሎት አድማሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማስፋት የተኝቶ ህክምናን ጨምሮ ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን የአገልግሎት ስብጥርና ጥራት በማሻሻል ከፍተኛ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ ነው፡፡...
Saterday, 13/ 11 /2016
የዘመቻ ስራው በጤና ቢሮ በተሰጠው የአመራር አቅጣጫ መሰረት እንደሴክተር በአስተዳደር ደረጃ የተከናወነው የፅዳት ዘመቻ አካል ነው።የፅዳት ዘመቻ ሥራው የስራ ከባቢን ፅዱና ምቹ ለማድረግ በጤና ጣቢያው ሠራተኞች በጋራ....
Monday, 07/ 06 /2016
ተቋማችን የደንገተኛ ቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠት የጀመረ..
Saterday, 08/ 06/ 2016
These are our surgical team members led by inetegrated emergency surgery professional..
Monday, 00/ 00 /00
We, Goro HC starts the following new diagnostic (imaging) services by senior specialist physician (Radiologist) using the latest version Doppler Ultrasound Machine. The services are:-...
Monday, 07/ 06 /2016
ጎሮ ጤና ጣቢያ የድንገተኛ ቀዶ ህክምናና በቀዶ ህክምና ማዋለድ አገልግሎት (C/S & Emergency Surgery) ለመስጠት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ሲሆን የድል ጮራ ሆስፒታል ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችል 8 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የቀዶ ህክምና ግብዓት ድጋፍ አድርጎልናል። ለተደረገልን ከፍተኛ ድጋፍ የድል ጮራ ሆስፒታልን እናመሰግናለን። በተለይም የሆስፒታሉ CEO ሙና ኢብራሂም በቀናነት ከመፍቀድ ጅምሮ ያንቺ ጉዳይ አድርገሽ ስራ ለማስጀመር የሚያስችል ግብዓት ለማሟላት ላደረግሽልን ቀና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን። ፈጣሪ ክብረት ይስጥልን!
የተሰጠበት ቀን:– 17/11/2016
1) የጤና ትምህርት ተሳታፊዎች ብዛት
ሴት= 36, ወንድ= 21, ድምር= 57
2) የተሰጠው ትምህርት ርዕሰ–ጉዳይ:
1. የወባ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር በተመለከተ እና
2. በግልና የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጧል።
3) ትምህርት የተሰጠበት ስራ ክፍል:ማዕከላዊ ትሪያጅ የተገልጋይ ወረፋ መጠበቂያ
4) ትምህርቱን የሰጠው ባለሙያ ስም: ሲር መሰረት መኮንን
በቀን 02/04/2016 ዓ.ም
በርካታ እስታፎቻችን የተሳተፉበት የደም ልገሳ ፕሮግራም ያዘጋጀን ሲሆን በዚህም በቅርብ የነበረው የዴንጊ ትኩሳት ተፅዕኖ ቢያሳድርብንም 22 units ደም መለገስ ተችሏል።
በቀን 01/04/2016 ዓ.ም
ተቋማችን ያለውን የወባ መከላከልና መቆጣጠር ያለበትን ደረጃ ለማየት የመጡ የ"USAID`` የጤና ሚኒስቴር ተወካዮችን ተቀብለን አስተናግደናል። በዚህም የወባ በሽታ
መከላከልና መቆጣጠር
ፕሮግራሞች ትግበራ እና የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና ረገድ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር አስረድተናል።
በቀን 05/24/2016 ዓ.ም
ቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ አዲስ የድንገተኛ ቀዶ ህክምናና በቀዶ ህክምና ማዋለድ (C/S & Emergency Surgery) አገልግሎት መስጫ ቴብል (New OR Table)
ሰጦናል።
በቀን 05/12/2016 ዓ.ም
የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከላከል ና ለመቆጠጣጠር ወረርሽኙ በተገኝበት አካባቢ የመከላከል ስራ ተሠርቷል
ዛሬ ቀን 29/03/2016 ዓ.ም
ሁለት ፕሮግራሞችን አንድ ላይ በማቀናጀት ከጠቅላላ እስታፎች ጋር አከናውነናል።
1ኛ) የተቋማችንን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግመናል።
በዚህም ሁሉም ኬዝ ቲሞችና ዲፓርትመንቶች አስተባባሪዎች የየክፍላቸውን የ3ወር አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በጋራ
ሰፊ ውይይት