Monday, 07/ 06 /2016
GHC BLOGS
ጎሮ ጤና ጣቢያ የድንገተኛ ቀዶ ህክምናና በቀዶ ህክምና ማዋለድ አገልግሎት (C/S & Emergency Surgery) ለመስጠት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ሲሆን የድል ጮራ ሆስፒታል ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችል 8 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የቀዶ ህክምና ግብዓት ድጋፍ አድርጎልናል። ለተደረገልን ከፍተኛ ድጋፍ የድል ጮራ ሆስፒታልን እናመሰግናለን። በተለይም የሆስፒታሉ CEO ሙና ኢብራሂም በቀናነት ከመፍቀድ ጅምሮ ያንቺ ጉዳይ አድርገሽ ስራ ለማስጀመር የሚያስችል ግብዓት ለማሟላት ላደረግሽልን ቀና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን። ፈጣሪ ክብረት ይስጥልን!
በቀን 02/04/2016 ዓ.ም
በርካታ እስታፎቻችን የተሳተፉበት የደም ልገሳ ፕሮግራም ያዘጋጀን ሲሆን በዚህም በቅርብ የነበረው የዴንጊ
ትኩሳት ተፅዕኖ ቢያሳድርብንም 22 units ደም መለገስ ተችሏል።
በቀን 01/04/2016 ዓ.ም
ተቋማችን ያለውን የወባ መከላከልና መቆጣጠር ያለበትን ደረጃ ለማየት የመጡ የ"USAID`` የጤና
ሚኒስቴር ተወካዮችን ተቀብለን አስተናግደናል። በዚህም የወባ በሽታ
መከላከልና መቆጣጠር
ፕሮግራሞች ትግበራ እና የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና ረገድ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር አስረድተናል።
በቀን 05/24/2016 ዓ.ም
ቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ አዲስ የድንገተኛ ቀዶ ህክምናና በቀዶ ህክምና ማዋለድ (C/S & Emergency
Surgery) አገልግሎት መስጫ ቴብል (New OR Table)
ሰጦናል።
በቀን 05/12/2016 ዓ.ም
የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከላከል ና ለመቆጠጣጠር ወረርሽኙ በተገኝበት አካባቢ የመከላከል ስራ ተሠርቷል
ዛሬ ቀን 29/03/2016 ዓ.ም
ሁለት ፕሮግራሞችን አንድ ላይ በማቀናጀት ከጠቅላላ እስታፎች ጋር አከናውነናል።
1ኛ) የተቋማችንን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግመናል።
በዚህም ሁሉም ኬዝ ቲሞችና ዲፓርትመንቶች አስተባባሪዎች የየክፍላቸውን የ3ወር አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በጋራ
ሰፊ ውይይት